Tag Archives: Blue Party

በአዲስ አባባ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ተወዳዳሪዎች

ሰማያዊ በከተማው ካስመዘገባቸው 23 እጩዎች ውስጥ ሊቀመንበሩን እና ሁለት ሴቶችን ጨምሮ አራት እጩዎች በእጣ ከተወዳዳሪነት ውጪ ሲሆኑ የተቀሩት ሁለት እጩዎች ደግሞ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት የተወዳዳሪነት መብታቻው ተገፏል!
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል

Mon, 03/03/2014

ዛሬ ጠዋት ልክ12 ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በመላው የሀገሪቷ ክፍል ለማንቀሳቀስና ለማጎልበት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን በሶስት አቅጣጫዎች ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ጉዞ ጀምሯል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ መገምገምና ለማጠናከር እንዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር ገምግሞ መፍትሄ መስጠትም አንዱ ሌላው የጉዞ አላማው ነው፡፡
የመስክ ጉበኝቱ በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡

ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

Visit the Official site here

የሰማያዊ ፓርቲ ትውውቅ በአሜሪካ

ዲሴምበር 15 2013 በዋሽንግተን ዲሲ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ተገኝተው ስለፓርቲያቸው እና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙርያ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ የእለቱ የክብር እንግዳ ፕ/ር አለማያሁ ገ/ማርያም ጽሁፍ ያቀርባሉ፡፡ እንዲሁም በተከታታይ በነዚህ ከተሞች ፓርቲውን የማስተዋወቁ ስራ ይቀጥላል::
Sunday, December 15 Washington, DC
Saturday, December 21 Atlanta, GA
Saturday, December 28 Houston, TX
Sunday, December 29 Dallas, TX
Saturday, January 04 San Jose, CA
Sunday, January 12 Seattle, WA