Tag Archives: Ethiopia

ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ

Semayawi- የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡

image

ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡
ዛሬ ሰኔ 9 2007 ዓ/ም በምስራቅ ጎጃም ጎንቻ ሲሶእነሴ ወረዳ ሰቀላ ገንቦሬ ቀበሌ አርባይቱ እንስሳ ቤተክርስቲያን ግብዓተ-መሬቱ ተፈፅሟል!
ፈጣሪ ለወንድማችን ነፍስ እረፍት አንዲሰጥ በሳሙኤል ህልፈተ ህይወት ልባችሁ ለተሰበረ ሁሉ መፅናናት እንዲሆን እንመኛለን!

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ

Negere Ethiopia

‹‹በኃይል የተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስት በህዝብ ተቀባይነት የለውም››

• ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል

• ‹‹የአፍሪካ ህብረት ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል የእንጨት ድስት ነው›› አቶ ስለሽ

image

ሰማያዊ ፓርቲ የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን እንደማይቀበለው አሳወቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ ግንቦት 21/2007 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ‹‹ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!›› በሚል ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ምርጫው ‹‹ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢ-ፍትኃዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፡፡›› ብሏል፡፡

በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ፓርቲም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን የገለፀው ሰማያዊ በሂደቱ የተሳተፈው የስርዓቱን ችግሮች ለማጋለጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹በሂደቱ ውስጥ በመቆየታችን እጩዎቻችን በህገ ወጥ መንገድ ሲታገዱ፣ ታዛቢዎች ሲከለከሉና ሲታሰሩ አሳይተናል፡፡ በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮም ሆነ በምርጫው ወቅት የነበረውን ማጭበርበር ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አጋልጠንበታል፡፡›› ብለዋል፡፡ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስለሽ ፈይሳ በበኩላቸው ምርጫው መትረየስ ተጠምዶ፣ ብረት ለበስ በየ መንገዱ ቆሞ፣ የአጋዚ ጦር አባላት ከተማ ውስጥ ተሰማርተው ከመካሄዱም ባሻገር ከፍተኛ የድምጽ ማጭበርበር የነበረበት ነው ብለዋል፡፡ የምርጫው ብቸኛ የውጭ ታዛቢ የሆነውን የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል ‹‹የእንጨት ድምጽ ነው!›› ሲሉ ተችተዋል፡፡

ምርጫው በህገ ወጥ አሰራሮች የታጀበ፣ በማንኛውም መመዘኛ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተአማኒ ሊሆን እንደማይችል ሒደቱ በግልፅ አመላካች ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በውጤቱም በሐገራችን የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ወደ መቃብር የከተተና ኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሐገር መሆኗን ያረጋገጠ ነው፡፡..ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የጨለማ ዘመን መምጣቱን ከማሳየቱ ባሻገር ኢህአዲግ በፍርሃት ተውጦ ሁሉንም ለመቆጣጠር ባደረገው ሩጫ ለመግለፅ እስኪያፍር ድረስ የሚያሸማቅቅ ውጤት እንዲከናነብ ሆኗል፡፡›› ብሏል፡፡ በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በሕዝብ ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጾአል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በአፈና እና ጭቆና ውስጥ ሆነው ድምጽ ለሰጡት መራጮች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ በምርጫው ሂደት የተንገላቱ፣ የታሰሩትን፣ የተደበደቡና የተሰደዱትን አባላቱንም ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን ለደረሰባቸው መከራና በደል ክብር ይገባቸዋል ብሏል፡፡ የዜጎች ነፃነት ሳይከበር ነጻና ፍትኃዊ ምርጫ ሊደረግ አይችልም ያለው መግለጫው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን እስከሚከበሩ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነጻነት ትግል ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጾአል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ይፋ አደረገ

በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፎች ይደረጋሉ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

image

የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ትብብሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብሩን በህዳር ወር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩ ደግሞ ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን ተገልጹዋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ፤ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳርና በአዳማ ደግሞ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) በመግለጫው ወቅት ተናግረዋል፡፡

‹‹የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር ነው›› ያለው መግለጫው፣ በትብብሩ በኩል በአመራር ከፊት ቆመው ትግሉን ለመምራት ዝግጁነትና ቁርጠኝነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡

‹‹የያዝነው የትግል መንገድ ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣ መጓጓዣችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን›› ብሏል ትብብሩ በመግለጫው፡፡

እቅዱ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ መሆኑን ያተተው የትብብሩ መግለጫ፣ ‹‹ዓላማችን የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ ሚናችንም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው›› ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡ ነጻነት በሌለበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው ሲልም አክሏል መግለጫው፡፡

ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት ማካተቱም ተመልክቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት፤ በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡

የትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ተግባራቱን በጊዜ ሠሌዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት ማጽደቁንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ትብብሩ ለያዘው ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ሌሎች ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በተፈጸመው አምባገነናዊ የጭካኔ እርምጃ ከትግላችን አናፈገፍግም!

ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ

በፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በተፈጸመው አምባገነናዊ የጭካኔ እርምጃ ከትግላችን አናፈገፍግም!

ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ዘጠኝ ትብብር የፈጠሩ ፓርቲዎች በህዳር ወር ያወጡት መርሐ ግብር አንድ አካል የሆነውን የ24 ሰዓት የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፍ ለመተግበር ሥራ ላይ የነበሩ አመራሮች፣ አባሎቻችና ደጋፊዎቻችን ላይ አምባገነኑ ስርዓት በወሰደው የግፍ እርምጃ ምክንያት ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው በጨለማ ክፍል ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
እስረኞቹ በጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል፣ አንድ ራሱን ‹‹መንግስት ነኝ›› የሚል አካል ‹‹እስር ቤት›› ብሎ ዜጎችን ሊያጉርበት ይችላል ተብሎ የማይጠበቅ ሽንት ቤትና ጋራዥ ውስጥ መታሰራቸው አልበቃ ብሎ በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ በድብደባው ምክንያት ራሳቸውን የሳቱና ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው አመራሮቻችን፣ አባላትና ደጋፊዎቻችን የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም፡፡ አገዛዙ ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው ለሰላማዊ ታጋዮች ባለው ጥልቅ ጥላቻና ጭካኔ በተሞላበት እርምጃው ከትግሉ ያፈገፍጋሉ ከሚል ስሌት ነው፡፡

ሆኖም እኛ ወደ ወደ ትግሉ ስንገባ ትግሉ ምን ያህል መስዋዕትነት እንደሚያስከፍል በሚገባ እናውቀዋለንና በየትኛውም መንገድ ስልጣኑን ለማስጠበቅ የሚጥረው ህወሓት/ኢህአዴግ መሰል የጭካኔ እርምጃ እንደሚወስድ የምንጠብቀው ነው፡፡ በመሆኑም አገዛዙ የወሰደውና ወደፊትም ሊወስደው የሚችለው ከዚህ የባሰም አረመኔነት የተሞላበት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል እንጅ ከትግላችን ቅንጣት ያህል ወደኋላ እንድናፈገፍግ የሚያደርገን አለመሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ አከብረዋለሁ እያለ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚጠቀምበትን ህገ መንግስት ራሱ እየናደው ‹‹ጅራፍ ራሱ ገርፎ..›› እንዲሉ ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀም ህጋዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የነበሩ አመራሮቻችን፣ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ላይ ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡ የሰልፉን ተሳታፊዎች ደብድቦና አፍሶ ባሰረበት ወቅት ‹‹ምንም ችግር ሳይፈጥሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል›› እንዳላለ ከስርዓቱ ቁጥጥር ያልወጣው የህግ አካል ‹‹መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት ወድሟል፡፡›› በሚል ሌላ ክስ አቅርቧል፡፡ ስርዓቱ ፓርቲያችንና ትብብሩ በጀመረው ሰላማዊ ትግል በመደናገጡ የሚይዘው የሚጨብጠው እንዳጣ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚዘውራቸው ተቋማት የተለያየ የፈጠራ ክስና ዘገባ ማቅረባቸው ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ፓርቲያችን በሚያደርጋቸው ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተገቢውንና አስፈላጊውን ውሳኔ እንደሚሰጥ መግለጽ ይወዳል፡፡ በዚህ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ግምባር ቀደም የሆኑ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት በእስር ለሚገኙና የህወሐት/ኢህአዴግ የግፍ ሰለባ ለሆኑ ጓዶቻችንና የትግል አጋሮቻችን ሁሉ ያለንን አክብሮት ስንገልጽ ምን ጊዜም ከጎናቸው እንደሆንንና ሰላማዊ ትግሉ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ ነው፡፡

ስለሆነም በሀገራችን ህዝባዊ ሥርዓት ለማምጣትና በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት ለመመስረት በምናደርገው ትግል ሁሉ የሚጠበቅብንን መስዋእትነት ለመክፈልና ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችን እየገለጽን መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀንለትና የምናከብረው ህዝብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት

ህዳር 30/2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ኑ! ራሳችንን ነጻ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!!!

የአ.አ አስተዳደር ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ

By Semayawi Party- Ethiopia 

• ‹‹ማስጠንቀቂያውን እንደ ቁም ነገር አንቆጥረውም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

• ‹‹ስርዓቱ ምን ያህል ዝቅጠት ውስጥ እንደገባ ያሳያል›› አቶ ግርማ በቀለ

image

image

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዳር 7/2007 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ያስተባበረው የ9ኙ ፓርቲዎች የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ፀረ ህገ መንግስት በመሆኑና ነዋሪዎችን ሰላምና ፀጥታ በማወኩ በቀጣይ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ካደረገ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ፡፡

አስተዳደሩ ትናንት ህዳር 11/2007 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ፤ ህዳር 6 ቀን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ለህዝብ የተሰራጨው በራሪ ወረቀት ህገ ወጥ መሆኑን፣ ህዳር 7/2007 ዓ.ም በኢንጅነር ይልቃል ጌትነት መሪነት ሊደረግ የነበረው አደባባይ ስብሰባ ህገ ወጥ እንደነበርና በወቅቱ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከፖሊስ ጋር ግብ ግብ ከመግጠማቸውም በተጨማሪ የአካባቢውን ህዝብ ሰላምና ፀጥታ አውከዋል ሲል ከሷል፡፡ አስተዳደሩ አክሎም ፓርቲው የአደባባይ ብጥብጥና ሁከት በመፍጠሩ እርምጃ እወስዳሉ ሲል ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ልኳል፡፡

በሌላ በኩል ሰማያዊ ፓርቲ በቀን 5/3/2007 ዓ.ም ለአስተዳደሩ የእውቅና ደብዳቤ ያስገባ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ አመራሮች አስተዳደሩ የላከው ደብዳቤ ከገዥው ፓርቲ ፍርሃት የመነጨ በመሆኑ ከእንቅስቃሴያቸው እንደማይገታቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብርና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ደብዳቤው ስርዓቱ የደረሰበትን መጠነ ሰፊ የፍርሃት ደረጃና ትግሉን ይበልጥ አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን የሚያሳይ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ማስጠንቀቂው የደረሰው ሰማያዊ ፓርቲና የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹የረዥም ጊዜ የመንግስት ታሪክ ባላት አገር የከተማ አስተዳደር ነኝ ያለ አካል እንዲህ አይነት ደብዳቤ መጻፉ ኢትዮጵያ ምን ያህል ውድቀት እንደገጠማትና እኛም እንደ ህዝብ የውረደት ካባ መከናነባችን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ እንደ ሰማያዊ አሊያም የትብብሩ ሊቀመንበርነት ሳይሆን እንደ አንድ ይህን ያህል ውርደት እንደገጠማት አገር ዜጋ ሀፍረት ይሰማኛል፡፡›› ሲሉ አስተዳደሩ የላከው ደብዳቤ ላይ አስተያየታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ማስጠንቀቂያው በቀጣይ የፓርቲውም ሆነ የትብብሩ እንቅስቃሴ ላይ የሚያመጣው ችግር ካለ በሚል ለኢንጅነር ይልቃል ላነሳነላቸው ጥያቄም ‹‹ደብዳቤው የኢህአዴግ ፍርሃት ገደብ መልቀቁንና ትግሉም ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት የሚያሳይ ነው፡፡ ኢህአዴግ ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴን ብቻ ሳይሆን የራሱን ጥላም አለማመን ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል፡፡ እኛ ይህን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደቁም ነገር አንቆጥረውም፡፡ ይበልጡንም ለትግሉ በተጠናከረ መንገድ ንድንነሳሳ ይገፋፋናል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የትብብሩ ፀኃፊና የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ማስጠንቀቂያው ትብብሩ በየሳምንቱ ያቀዳቸውን መርሃ ግብሮች ለማደናቀፍ ያለመ ነው፡፡ ከአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት እንዲህ አይነት አሳፋሪ ደብዳቤ መጻፉ ስርዓቱ ምን ያህል ዝግጠት ውስጥ እንደገባ ያሳያል፡፡ ሆኖም ማስጠንቀቂያው ከእንቅስቃሴያችን አይገታንም፡፡ እንዲያውም ለዚህ የስርዓቱ ዝቅጠት የሚመጥን ስልት ነድፈን በጋራ እንድንሰራ ያደርገናል፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል

Mon, 03/03/2014

ዛሬ ጠዋት ልክ12 ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በመላው የሀገሪቷ ክፍል ለማንቀሳቀስና ለማጎልበት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን በሶስት አቅጣጫዎች ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ጉዞ ጀምሯል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ መገምገምና ለማጠናከር እንዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር ገምግሞ መፍትሄ መስጠትም አንዱ ሌላው የጉዞ አላማው ነው፡፡
የመስክ ጉበኝቱ በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡

ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

Visit the Official site here

እናቴን ምከሯት (አሌክስ አብረሃም)

እናቴን ምከሯት
(አሌክስ አብረሃም)

የዘመን ስፍራችሁ
ለምክር የደረሰ
የእውነት መብረቃችሁ
ድቅድቅ ጨለማዋን
ደፍሮ የገመሰ

እናቴን ምከሯት
ዝከሯት ካሁኑ
ዘመን ሳይደነግዝ
ሳይጨላልም ቀኑ
በነጠላዋ ጫፍ
ታስቀምጠው ቋጥራ
ቢያሻት ቃሉን ትትፋው
ትጣለው አንቅራ
ብቻ ….
ምከሯት …. ምከሯት…..
ምከሯት እናቴን …
ወይ ጠርታ ትቀፈኝ
ወይ ትላክ እትብቴን

እጆቿን ወደእግዜር
መዘርጋቷን ትታ
ትጀነን ይዛለች …..
ቀዳዳ ኪሶች ውስጥ
ባዶ እጆቿን ከታ

እጅን የፈጠረ
ፀንተው ለዘረጉ እጁ መች አጠረ
እላለሁ ለእማማ
ጆሮዋ ደንድኖ
ልጆቿን ባትሰማ

ፊተኞች ከኋላ
ኋለኞቹ ከፊት ሲገለባበጡ
‹‹ቀን ይመጣል›› ማለት
ከሰልፍ እየወጡ
ማላገጥ ነው በሏት
ጆሮሽ ስለራሱ
ሰርክ ቢሆን ባዳ
እስከመቸ ልጅሽ
አንችን እየሸሸ
ይኑር ምድረ በዳ ?

እይውልሽ እማ …..
የጣፈጠ በልተው
ያማረ ቢለብሱ
ከልጅ ልጅ ለይተው
አመትም አይደርሱ
ብያለሁ ንገሯት

ያገባትን ሁሉ
‹‹አባት በል›› አትበለኝ
በእናቴ ስም ልኩራ
በእናቴ ሰው ልሁን
በእናቴ ልጠራ

ያባት አባትነት
ላገባት እናቴ
ባል ሁኖ መገኘት
እንጅ በባል ካባ ስለተጀቦነ
ከመቸ ወዲህ ነው
እናቴን ነጣቂ
ባል አባት የሆነ?
በሉልኝ ለእማማ

ልጅሽ መቀመጫው
እንደ እህል ቢርበው
ከእግዜሩ ተጣልቷል….
‹‹የለት እንጀራህን አልፈልግልህም
የለት ማረፊያየን እናቴን›› እያለ
ፆሎቱን አናግቷል

በሉልኝ እናቴን

ደግሞ እንደምትሏት ……..
‹‹እንግዳ ተቀባይ …
ምናምን ነኝ ››እያልሽ
ታወሪያለሽ አሉ
ቆይ ጊዜ ለኩሉ !!
ብያለሁ ንገሯት ……

ቤት ለእንግዳ ማለት
ኗሪውን እንግዳ
እያረጉ አይደለም
ያለልጅ ፈገግታ
‹ዘ ፀዓት› ይሉት ቀን
አልነበረም የለም
በሉልኝ ለናቴ ……

ምከሯት …. ምከሯት…..
ምከሯት እናቴን …
ወይ ጠርታ ትቀፈኝ ወይ ትላክ እትብቴን